የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢንያም መንገሻ ፤ በክልሉ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ9 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሰላም መጥተዋል ብለዋል።
አቶ ቢንያም ባለፉት አራት አመታት በክልሉ እንደ ፋኖ፣ኦነግ ሸኔ፣ጉሂዲኒ እና ቤኒን ባሉ የታጠቁ አካላት ምክንያት ሰፊ ግጭት ነበር ሲሉ ተናግሯል።
ሃላፊው በተለይ እዛው ክልል ውስጥ ባሉ በጉሂዲኒ እና ቤኒን ባሉ የታጠቁ አካላት ግጭት ምክንያት በሰዎችና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል።
አሁን ላይ በፌዴራልና በክልሉ መንግስት እንዲሁም በሀገር ሽማግሌ በተሰራ ስራ፥ ሁለቱን ጎሳዎች አስታርቆ ከ9 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።
ወጣቶቹን በክልሉ ባሉ 537 ማህበራት በማደራጀት፤ በእርሻ ስራ፣በወርቅ ቁፋሮ፣በከተማ ንግድ ተደራጅተው እንዲሰሩ እድል ተመቻችቷል ብለዋል።
የክልሉ መንግስት ለስራው የሚያገለግሉ 48 የእርሻ ትራክተሮሪ፣31 የወርቅ ማጠቢያና መቆፈሪያ ማሽኖች፣በበጋ ወቅት መስኖ ለመስራት የሚያገለግሉ 50 ፓንፖችና ጄኔሬተሮችን ማቅረቡን ጠቁመዋል።
የቢሮ ኃላፊ አሁንላይ እንቅስቃሴና ስራን የሚገድብ የሰላምና ፀጥታ ችገር የለም ያሉ ሲሆን ፤አንዳድ ግለሰቦችና ቡድኖች አሁንም እንደሚኒቀሳቀሱ ግን ተናግረዋል።
ክልሉን ከስጋት የፀዳ ለማድረግ አሁንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ወደ ሰላም እንዲመጡ እንሰራለን ብለዋል።
ልኡል ወልዴ
የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም
