ዓለም ዓቀፍ የህክምና ግብዓት አቅራቢዎች ጉባዔ ሊካሄድ ነዉ፡፡

የህክምና አገልግሎት ቴክኖሎጂዎችን የሚያቀርቡ ኩባንያዎች የሚገኙበት የኢትዮ ኸልዝ አውደ-ርዕይ ሊካሂድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሚዘጋጀዉ 4ኛዉ አለም አቀፍ የአቅራቢዎች ጉባኤም ከኢትዮ ኸልዝ አውደ-ርዕይ ጎን ለጎን የሚካሄድ ነዉ፡፡

በዘንድሮዉ ዓመት ከ20 በላይ የሙያ ማህበራትና ከአጋር ድርጅቶች ጋር የሚዘጋጁ 40 የሚሆኑ ጉባኤዎችና ስልጠናዎች እንደሚካሄዱም ተገልጿል፡፡

በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ያለዉን የህክምና አገልግሎት ፍላጎት የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን በሚያቀርቡ 10 አገራት ላይ መሠረታቸዉን ያደረጉ ኩባንያዎችም ይገኛሉ ተብሏል።

ከ4ሺህ በላይ የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የንግድ ሰዎች ከዓለም ዓቀፍ እና የሃገር ዉስጥ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ትስስር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አውደ-ርዕዩ ለ 9ኛ ጊዜ ከየካቲት 13 እስከ 15 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *