በኦሮሚያ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ሕይወት አለፈምስራቅ ወለጋ ዞን ጉዳያ ቢላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው ከሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡

በደረሰው አደጋም የ26 ሰዎች ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 42 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዞኑ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር አስናቀ መስፍን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *