በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ከሜዳው ውጪ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ ፣ ብራሂም ዲያዝ እና ጁድ ቤሊንግሀሞ አስቆጥረዋል።
ማንችስተር ሲቲን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2 ከመረብ አሳርፏል።
ቪንሰስ ጁኒየር የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መመረጥ ችሏል።
በሌሎች ጨዋታዎች
ጁቬንቱ ከፒኤስቪን 2ለ1 ፣ቦርስያ ዶርትመንድ በበኩሉ ከስፖርቲንግ ሊስበንን 3ለ0 ማሸነፍ ችሏል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
