የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 43 በመቶ የወንጀል ሁነቶችን መቀነስ ችያለሁ አለ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ 43 በመቶ ወንጀሎች ቀንሰዋል ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ወንጀልን ከመከላከል አንፃር ካለፉት አመታት በተለየ መልኩ በቴክኖሎጂ ታግዘዉ ስራዎች በመሠራታቸዉ ለወንጀሉ መቀነስ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማዉን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ሀላፊነቱን እየተወጣ ነዉ ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ሃላፊነት በመዉሰድ ስራዎችን እየሰራ ቢሆንም የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲያመጣ ማህበረሰቡም ሊደግፈዉ ይገባል ነዉ ያሉት፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኮሚሽኑ ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑንም ኮማንደር ማርቆስ ነግረዉናል፡፡

ሰሞኑን አዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለማካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉንም ገልፀዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

የየካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *