ንብ ኢንተርናሺናል ባንክ የዲጂታል የክፍያ ስርዓትን ይፋ  አደረገ።

ንብ ኢንተርናሺናል ባንክ “አምበር ፔይና ንብ ፔይ ስትሪም” የተሰኘ የዲጂታል የክፍያ ስርዓት ይፋ አድርጓል።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለደንበኞቹና ለባንክ ተገልጋዮች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያግዛል ያለውን “አምበር ፔይና ንብ ፔይ ስትሪም “የተሰኘውን የዲጂታል የክፍያ ስርዓትን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።

የንብ ኢንተርናሺናል ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ፤ፕሮጀክቶቹ በዲጅታል ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ጉልህ ሚና እንድንጫወት ይረዳናል ብለዋል።

የዲጅታል መተግበሪያዎቹ ተገቢው የደህንነት ፍተሻ እንደተደረገላቸውም ገልፀዋል።

አቶ ሄኖክ እንዳሉት “ንብ አምበር ፔይ” በንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ የባንካችን ደንበኞች ለሚስጡት አገልግሎት ከደንበኞቻቸው የሚከፈሉ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመቀበል ያግዛቸዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ  የተቀመጠው የኪው አር ኮድ(QR.Code ) ስርዓት በንብ ፔይ ስትሪም አገልግሎቱን ማስጀመራቸውን አስታውቋል ።

ይህም አገልግሎት አቅራቢዎች ክፍያቸውን ከየትኛውም ባንክ  በቀላሉ ለመቀበል ያስችላቸዋል ነው ያሉት::

ባንኩ ጊዜው የደረሰባቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እየተከታተለ ሥራ ላይ ማዋሉን እንደሚቀጥል ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡

ልኡል ወልዴ

የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *