የታቀደዉና ወደ አገር ዉስጥ እየገባ ያለዉ ኮንዶም ሊመጣጠን አለመቻሉ ለዚህ እንደ ምክንያትነት የተጠቀሰ ጉዳይ ነዉ፡፡
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኤድስ ሄልዝኬር ፋዉንዴሽን ዋና ዳይሬክተር ቶሎሳ ኦላና፤ በአገራችን አሁንም የኮንዶም ዕጥረት አለ ብለዋል፡፡
ከ2መቶ70 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ለኤችኤይቪ እና ለሌሎች ህመሞች ተጋላጭ ናቸዉ ተብለዉ ለተለዩ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ሊደርስ እንዳልቻል ተናግረዋል።
ድርጅቱ በየዓመቱ ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጋ ኮንዶም ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ ቢሆንም፤ በኮንዶም ስርጭት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡት የኮንዶም ቁጥር ተደምሮ የሀገሪቱን የኮንዶም ፍላጎት መሙላት አልተቻለም ነዉ ያለዉ።
አሁን ላይ እንደ ችግር እየታየ ያለዉ ፈንድ የሚደረገዉ ገንዘብ ነዉ ያሉት አቶ ቶሎሳ፤ አጋር ድርጅቶቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ድጋፋቸዉን እየቀነሱ በመሆኑ አገራችን የምትፈልገዉን ያህል ኮንዶም እያገኘች አይደለም ብለዋል፡፡
ነገሮች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ ኢትዮጰያ ዉስጥ ካሉ ድርጅቶች ጋር አንድ ላይ ለመሠራት መታቀዱንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ሶስት ዋና ዋና ኮንዶም አቅራቢዎች ሲኖሩ በግሎባል ፈንድ የሚደገፈዉ እና ኮንዶሞችን በመላዉ አገሪቱ ላሉ ጤና ጣቢያዎች በነጻ የሚያከፋፍለዉ የፋርማሲዩቲካል ኤጀንሲ ነዉ፡፡
ሁለተኛው አቅራቢ ዲኬቲ ኢትዮጵያ ሲሆን ኮንዶም በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ መሆኑ ይገለጻል፡፡
ሶስተኛው የቅንጦት ኮንዶም የሚያስገቡ የግል ኩባንያዎች ናቸዉ፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
