ሰዎች በአባላዘር በሽታ በሚጠቁበት ጊዜ በተለያዩ የካንሰር አይነቶች የመያዝ ዕድላቸዉ 15 በመቶ ከፍ እንደሚልም ነው የተገለጸው።
በአለም አቀፍ ደረጃ በቀን ዉስጥ ከ 1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በአባላዘር በሽታ እንደሚያዙም ሰምተናል።
በአገራችንም በተሰራ ጥናት በህመሙ ከሚያዙ ሰዎች አራቱ ህይወታቸው ያልፋል።
ኤች አይቪን፣ እርግዝናን እንዲሁም የአባላዘር ህመምን መከላከያ የሆነዉ ብቸኛዉ ኮንዶም ነዉ የሚሉት የኤድስ ሄልዝኬር ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር ቶሎሳ ኦላና፤ በተለይ የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል ብቸኛዉ አማራጭ መሆኑን ገልፀዋል።
በህመሙ ዙሪያ ኢትዮጵያን መሠረት ያደረጉ ዳታዎችን ለመሰብሰብ እየተሰሩ ያሉ ተጨማሪ ጥናቶች እንዳሉም አቶ ቶሎሳ ተናግረዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም
