88ኛው የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን እየታሰበ ይገኛል።

የዛሬ 88 አመት ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በጦር አዛዡ ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ ቦንብ ወርውረው ጉዳት ማድረሳቸውን ተከትሎ የጣሊያን ጦር የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም 30 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በግፍ መጨፍጨፉን ታሪክ ይነግረናል፡፡

በዚህ ቀን ወጣቶች፣ የጦር መኮንኖች፣ ካህናትና ሌሎችም ካሉበት እየተለቀሙ በግፍ ተጨፍጭፈዋል፡፡

ለሰማዕታቱ መታሰቢያ ይሆን ዘንድም በስድስት ኪሎ የመታሰቢያ ሀውልት ቆሞ ይገኛል፡፡

የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *