አዲስ አበባ የበጀቷን 71 በመቶ ለዘላቂ ልማት፣ ደህነት ለመቅረፍና የህዝቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል እያዋለች መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ላይ የግማሽ ዓመቱን አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ከንቲባዋ የገቢና ወጪ መጣጣም ብሎም እድገቱ ከተማዋ ምን ያህል በፈጣን ለውጥ ውስጥ እንደሆነች ተጨባጭ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ111 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

125 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 111 ነጥብ 5 ተሰብስቧል ብለዋል፡፡ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ37 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብልጫ መመዝገቡን ገልጸዋል፡፡

ባለፉት 6 ወራት 125.5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 111.5 (90%) ተሰብስቧል ካሉ በኃላ የገቢ አሰባሰባችን አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው 74.3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር በ37.2 ቢሊዮን ብር (በ50%) ምርታዊ እድገት አሳይቷል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩን ሀብት አመዳደብና አጠቃቀም ውጤታማነትን ለማሳደግ የበጀት ድልድል የከተማ አስተዳዳሩን የትኩረት አቅጣጫዎች በመለየት ለዘላቂ ልማት ዘርፎች መደልደሉን አሳውቀዋል። በዚሁ መሰረት ለዘላቂ ልማት የሚመደበውን የመንግስት በጀት በ2016 ከነበረበት 60% ወደ 71% ታቅዶ አፈፃፀሙ 71% መድረስ መቻሉን አንስተው፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ ስርአት ውስጥ መግባት እየተገባቸው ያልገቡትን 8,450 የንግድ ተቋማትን ወደ ቫት ስርአት እንዲገቡ በመደረጉና የታክስ ኦዲትና ሽፋንና ውጤታማነት ለማሻሻልና ለማስፋት ከፍተኛ ስራ መሰራቱን አንስተዋል፡፡እንዲሁም በመርካቶና በከተማዋ በሚገኙ ትልልቅ የንግድ ቦታዎች የተሰራው የቁጥጥርና ህግ የማስከበር ስራ ገቢ ከማሳደግ ባሻገር ፍትሃዊነት እንዲሰፍን አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል በሪፖርታቸው፡፡

የገቢና ወጪ መጣጣምና እድገቱ የከተማዋ ምን ያህል ፈጣን ለውጥ ውስጥ እንደሆነች አንዱ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የበጀቱ 71 እጁ ለዘላቂ ልማት፣ ደህነት ለመቅረፍና የህዝቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል መዋሉ ምን ያክል ለከተማዋ ነዋሪዎች ትኩረት እንደሰጠንና በታማኝነት እያገለገልን መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉም ተደምጠዋል ፡፡

የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *