ይህ የተናገሩት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሥድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነው ።
“በአዲስ አበባ ከተማ አሁን ላይ ምንም አይነት ግብርን አልጨመርንም“ ሲሉ የገለጹት ከንቲባዋ፤ እያደረግን ያለነው የታክስ መሰረቱን ማስፋት ነው ያም ነው ገቢያችን እንዲጨምር ያደረገው ብለውል፡፡
እነ መርካቶ ለግብር የሚፈሩ እና የማይሞከር ቦታ የነበሩ ግብር የሚከፍለው ነጋዴ የሚጎዳበት እና የማይከፈለው የሚከብርበት ነበር ብለዋል፡፡
አጠቃላይ ከመርካቶ የሚከፋፈለው ሸቀጥ የሃገርን የግብር ስርዓት ሲያናጋ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በመጠኑም ቢሆን ማስተካከል ችለናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
አሁንም አልቋል ተጠናቋል ባንልም ግን ለውጥ ማየት ችለናል ሲሉም ከንቲባ አዳነች ለምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል፡፡
በከተማዋ ከ4ሺ በላይ የሆኑ በተጨማሪ እሴት ታክስ ውጪ የነበሩት የግል ድርጅቶች በተጨማሪ እሴት ታክስ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓልም ብለዋል፡፡
ካፒታላቸውን እንዲከፍሉ የሚያስገድዳችው ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ግብር አይከፍሉም ነበር ስርዓቱ ውስጥም አልገቡም ነበር አሁን ላይ ግን በተጨማሪ እሴት ታክስ ስርዓት ውስጥ አስገብተናቸዋል ብለዋል፡፡
ከግል ድርጅቶች በትክክል ግብር አላገኘንም ነበር ለእኛ አይከፍሉንም ነበር ይህንን በኦዲት ነው ያረጋገጥነው ገንዘቡም ለሰራተኞቸሁ አይቀረም ነበር እሱን በማስተካከል ነው የከተማውን ገቢ ያሳደግነው ሲሉም ለአባላቱ አስረድተዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
