በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የሎስ ብላንኮዎቹን ሶሰቱንም የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለማንችስተር ሲቲ ኒኮ ጎንዛሌዝ አስቆጥሯል።
ሪያል ማድሪድ ጨዋታውን በድምር ውጤት 6ለ3 በማሸነፍ አስራ ስድስቱን ተቀላቅለዋል።
በሌላ ጨዋታ ፒኤስጂ ከብሬስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ 7ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።
ፒኤስጂ ጨዋታውን በድምር ውጤት 10ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።
ቦሩሲያ ዶርቱመንድ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ 16ቱን ለመቀላቀል ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3-0 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።
ፒኤስቪም 16ቱን ለመቀላቀል ከ ጁቬንቱስ ጋር ያደረጉውን የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 4-3 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።
ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
የሊቨርፑልን ግቦች መሐመድ ሳላህ እና አሌክሳንደር አርኖልድ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለአስቶን ቪላ ዋትኪንስ እና ቴሌማንስ አስቆጥረዋል።
ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በውድድር አመቱ ሀያ አራተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
