ከዚህ ቀደም ለጣቢያችን ቅሬታ ያቀረቡ ታካሚዎች ከሁለት ሳምንት በኋላ ተመልሳችሁ ኑ መባላቸውን እና ተመልሰው ቢሄዱም ማሽኑ በመበላሸቱ እንደውልላችኋለን መባላቸውን ነግረውን ነበር።
በወቅቱ በሆስፒታሉ ቁጥር በተደጋጋሚ ብንደዉልም ቁጥሩ አይሰራም የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፤በተደጋጋሚ እየሄድን ማሽኑ መች እንደሚሰራ ንገሩን ብንልም መልስ የሚሰጠን አካል ማግኘት አልቻልንም ብለው ነበር።
ጣቢያችንም የታካሚዎችን ቅሬታ ይዞ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱረዛቅ መሀመድ ደውሎ ነበር፤ እርሳቸው እንደተናገሩት ከአንድ ወር በፊት አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረዉ ማሽን ባሳለፍነዉ ሳምንት ታካሚዎችን መቀበል ችሏል።
አሁን ላይ ሆስፒታሉ እየተጠቀመበት የሚገኘዉ አንድ ማሽን መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር አብዱረዛቅ ፤ማሽኑ መበላሸቱ ሆስፒታሉ ተጨማሪ ማሽን እንደሚያስፈልገዉ ማሳያ ነው ብለዋል።
ለካንሰር ህመም የሚሰጠው የጨረር ህክምና ከተጀመረ በኋላ መቋረጥ የለበትም የሚሉት ዶ/ር አብዱረዛቅ፤ ጤና ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ቃል የገባልንን ማሽን እንደ ትልቅ ተስፋ እየጠበቅን እንገኛለን ብለዋል።
የካንሰር ህክምና ትልቅ ወጭ የሚጠይቅ እና ብዙ ድጋፍ የሚያስፈልገው ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በተለያዩ የባለድርሻ አካላት ሊደገፍ እንደሚገባውም ተናግረዋል።
ሊዲያ ደሳለኝበጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከወር በፊት አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረው የጨረር ማሽን መስራት መጀመሩ ተገለፀ።
ከዚህ ቀደም ለጣቢያችን ቅሬታ ያቀረቡ ታካሚዎች ከሁለት ሳምንት በኋላ ተመልሳችሁ ኑ መባላቸውን እና ተመልሰው ቢሄዱም ማሽኑ በመበላሸቱ እንደውልላችኋለን መባላቸውን ነግረውን ነበር።
በወቅቱ በሆስፒታሉ ቁጥር በተደጋጋሚ ብንደዉልም ቁጥሩ አይሰራም የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፤በተደጋጋሚ እየሄድን ማሽኑ መች እንደሚሰራ ንገሩን ብንልም መልስ የሚሰጠን አካል ማግኘት አልቻልንም ብለው ነበር።
ጣቢያችንም የታካሚዎችን ቅሬታ ይዞ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱረዛቅ መሀመድ ደውሎ ነበር፤ እርሳቸው እንደተናገሩት ከአንድ ወር በፊት አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረዉ ማሽን ባሳለፍነዉ ሳምንት ታካሚዎችን መቀበል ችሏል።
አሁን ላይ ሆስፒታሉ እየተጠቀመበት የሚገኘዉ አንድ ማሽን መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር አብዱረዛቅ ፤ማሽኑ መበላሸቱ ሆስፒታሉ ተጨማሪ ማሽን እንደሚያስፈልገዉ ማሳያ ነው ብለዋል።
ለካንሰር ህመም የሚሰጠው የጨረር ህክምና ከተጀመረ በኋላ መቋረጥ የለበትም የሚሉት ዶ/ር አብዱረዛቅ፤ ጤና ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ቃል የገባልንን ማሽን እንደ ትልቅ ተስፋ እየጠበቅን እንገኛለን ብለዋል።
የካንሰር ህክምና ትልቅ ወጭ የሚጠይቅ እና ብዙ ድጋፍ የሚያስፈልገው ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በተለያዩ የባለድርሻ አካላት ሊደገፍ እንደሚገባውም ተናግረዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም
