ዘለኒስኪ ሥልጣኔን ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ አሉ፡፡

የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ ለአገራቸው ሠላም የሚያመጣ ከሆነ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቀዋል።

ይህን ምርጫ ዘለንስኪ ያቀረቡት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ሙሉ ጦርነት የጀመረችበትን የሶስት አመት መታሰቢያ ዋዜማ አስመልክቶ በኪየቭ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት “የኔ ከሥልጣን መልቀቅ ሠላም የሚያመጣ ከሆነ ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ” ብለዋል።

ከሥልጣን የሚለቁት ግን አገራቸው በምላሹ የኔቶ አባል የምትሆን ከሆነ ብቻ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዘለንስኪና እና ትራምፕ መካከል ያለው አለመግባባት እየሰፋ መሄዱ ፣ለዘለኒስኪ እንዲህ ያለ አማራጭ አንዱ ምክንያት ነው እየተባለም ይገኛል።

የቀድሞው ኮሜዲያን እና የአሁኑ የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ የኔቶን አባልነት የማያገኙ ከሆነ የሠራዊታቸው ቁጥር በእጥፍ ማደግ እንደሚኖርበት መናገራቸው አይዘነጋም።

ልኡል ወልዴ

የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *