በአዲስአበባ ከተማ ከ ሀምሌ ወር ጀምሮ አስከ የካቲት ወር አጋማሺ የጣራ እና ግድግዳ ግብር አሰባሰብ ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ መገኘቱን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል
በስድስት ወር የግብር ስብሰባ አፈፃፀም 62 ከመቶ ግብር ከፋዬች ግብር እንደከፈሉ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰዉነት አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ፡፡
ከቦታ እና ከቤት ጋር የተያያዘ ዉዝፍ እና የዘንድሮዉ አመት አጠቃላይ ከ 6 ቢሊዬን ብር በላይ ግብር መሰብሰቡን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ገልፀዋል ፡፡
የጣራ እና ግድግዳ ግብር እስከ የካቲት 30 ያልከፈሉ ነዋሪዎች የ 5 በመቶ ቅጣት እስከ እነ ወለዱ እንደሚከፍሉ አስጠንቅቀዋል ፡፡
ግብር ያልከፈሉ የተሰጣቸውን ጊዜ በመጠቀም በአግባቡ እንዲከፍሉ አቶ ሰዉነት አየለ አሳስበዋል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም
