በ27ተኛ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐግብሮች አርሰናል ነጥብ ሲጥል ሊቨርፑል፣ማንችስተር ሲቲ እና ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፍ  ችሏል ።

ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የሊግ ጨዋታ ሊቨርፑል 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ማክ አሊስተር እና ዶምኒክ ስቦዝላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ ከተከታዩ አርሰናል ያላዉን የነጥብ ልዩነት ወደ አስራ ሶስት ማስፋት ችለዋል።

አርሰናል ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከኢፕስዊች ታውን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የማንችስተር ዩናይትድን ግቦች ሀሪ ማጓየር ፣ ዴሊት እና ሞርሲ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኢፕስዊች ሁለቱንም ግቦች ጃደን  አስቆጥሯል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ በኤርሊንግ ሀላንድ ግብ 1ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ 20ኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

በሌላ ጨዋታ ብሬንትፎርድ ከኤቨርተን ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የሊግ ደረጃቸው

1 ሊቨርፑል:- 67 ነጥብ
2 አርሰናል :- 54 ነጥብ
3 ኖቲንግሀም ፎረስት :- 48 ነጥብ
4 ማንችስተር ሲቲ :- 47 ነጥብ
5 ቼልሲ:- 46 ነጥብ
6 ኒውካስል ዩናይትድ :- 44 ነጥብ
13 ቶተንሀም    :- 33 ነጥብ
14  ማንችስተር ዩናይትድ :- 33 ነጥብ

ጋዲሳ መገርሳ

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *