ሃማስ የአራት ታጋቾችን አስከሬን ካስረከበ በኋላ እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን ፈታች።

ሃማስ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች ምትክ የአራት እስራኤላውያንን የጋዛ ታጋቾች አስከሬን አስረክቧል፡፡

እ.ኤ.አ. በጥቅምት 7 ቀን 2023 አድርሱት በነበረው ድንገታዊ ጥቃት በሃማስ የተወሰዱት የአራቱን ዜጎቿን አስክሬን ለማረጋገጥ ምርመራ እንደምታደርግ እስራኤል አሳውቃለች፡፡

ሃማስ የአራቱን ታጋቾች አስከሬኖች ያስረከበው ህዝብ ሳይሰበሰብና የመድረክ ትዕይንት ሳያዘጋጅ ሲሆን እስራኤል መሰል ዝግጅቶች ከተደረጉ እስረኞችን አለቅም በሚል ማስጠንቀቋ ዋነኛው ምክንያት እንደሆነም ተዘግቧል፡፡

እስራኤል የፍልስጤሙ ቡድን ታጋቾችን ሲያስረክብ “የዜጎቼን ክብር ዝቅ የሚያደርግ” ዝግጅት ማካሄድ የለበትም በሚል ባለፈው ሳምንት ልትለቃቸው የነበሩ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ሳትፈታ መቆየቷ ይታወሳል።

በግብጽ አደራዳሪነት በተደረሰው ስምምነትም ዛሬ ማለዳ ላይ እስራኤል ከ600 በላይ የፍልስጤም እስረኞችን መልቀቅ የጀመረች ሲሆን አብዛኛዎቹም ወደ ዌስት ባንክ እና ጋዛ ሲመለሱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከአደባባይ በመውጣት በደስታ እንደተቀበሏቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ለሰባት ሳምንታት በዘለቀው የመጀመሪያ ምዕራፍ ስምምነት ሃማስ 34 በህይወት ያሉ እና 10 የታጋቾች አስከሬን አስረክቧል፤ እስራኤል ደግሞ ዛሬ የምትለቃቸውን ጨምሮ 1700 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።

ቀሪዎቹን 59 ታጋቾች ለማስለቀቅ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መራዘም ይኖርበታል።

እስራኤልና ሃማስ በጥር ወር መጨረሻ የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ የፊታችን ቅዳሜ ይጠናቀቃል።

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *