በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚደርሰው ዝርፊያ እና ውድመት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት አሳወቀ፡፡

በአጥፊዎች ላይ ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ እየተወሰደ ባለመሆኑ የስርቆት ወንጀሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

ከሰሞኑ በአምቦ፣ ደሴ፣ ጎንደርና ወልድያ ሪጅኖች ላይ በተፈፀመ ስርቆት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንቦኞችን ከማጉላላቱም ባሻገር ከ16 ሚሊዮን 8 መቶ 60 ሺ ብር በላይ የሚገመት የንብረት ጉዳት መድረሱን አገልግሎቱ ገልጻል፡፡

በዚህም በአምቦ ሪጅን ብቻ 8 የተለያየ አቅም ያላቸው የዲስትሪቡሽን ትራንስፎርመሮች፤ በወልድያ፣ ጎንደርና ደሴ ከ5 በላይ ከፍተኛ የኤሌክተትሪክ አስተላላፊ መስመር ተሸካሚ ታወሮች ላይ ስርቆት ተፈፅሟል፡፡

በአጥፊዎች ላይ ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ እየተወሰደ ባለመሆኑ የስርቆት ወንጀሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ገልቷጻል፡፡

ተቋሙ በተለያዩ ጊዚያት የዲስትሪቡሽን ትራንስፎርመሮች፣የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮችና ታወሮች ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች ዝርፊያና ውድመት እየተፈፀመ በመሆኑ የኤሌክትሪክ የተደራሽነትን ማስፋት በሚያደርገው ጥረት ላይ ተግዳሮት እየሆነ እንደመጣበት አመልክቷል፡፡

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *