እስራኤል ወደጋዛ ሰብዓዊ እርዳታ እዳይገባ ማድረጉዋ የፍልስጤምን ሉአላዊነት የሚጋፋ ነው ስትል ደቡብ አፍሪካ አስታወቀች

ሃገሪቱ እንዳለችው እስራኤል ወደ ጋዛ ሰብዓዊ እርዳ እዳይገባ ማገዱዋና በዌስት ባንክ የምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ የፍልስጤምን እራስን የማስተዳደር መብት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ስል አውግዛለች፡፡

ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ መከልከል የተኩስ አቁም ስምምነቱንና አለማቀፍ የሰብዓዊ ህግን የሚጥስ ነው ስትል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩዋ በኩል አስታውቃለች፡፡

ሃገሪቱ ጨምራም እስራኤል በጋዛ ላይ ረሃብን እንደጦርመሳሪያ እየተጠቀመች የዘር ማጥፋ እየፈጸመች ነው ብላለች፡፡

በጥቅምት ሰባት 2023 የሃማስ ጥቃት መነሻነት እስራኤልና ሃማስ በጋዛ ባደረጉት ጦርነት እስካሁን ከ 48ሺ በላይ ፍልስጤማውያን እንደሞቱ ዘገባዎች ያሳያሉ ዘገባው የአናዱሉ ነው፡፡

ገነነ ብርሃኑ

የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *