የደቡብ ኮሪያ ፍርድ ቤት ከማርሻል ህግ ድንጋጌ ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮል ከእስር እንዲፈቱ አዟል።
ፍርድ ቤቱ ሪፖርቶቹን ወዲያውኑ ባያረጋግጥም ፤የሴኡል ማዕከላዊ አውራጃ ፍርድ ቤት ውሳኔውን አሳልፏል ሲል አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በጥር ወር ከማርሻል ህግ ድንጋጌው ጋር በተያያዘ መያዛቸዉ ይታወሳል፡፡
አዋጁ አመፅ ነው ሲሉ መርማሪዎች ክስ ያቀረቡ ሲሆን፤ ጥፋተኛ ሆነዉ ከተገኙ የሞት ቅጣት ወይም የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል ተብሎ ነበር።
ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤቱ የፕሬዝዳንቱን ጥፋተኝነት ካረጋገጠ፤ በይፋ ከቢሯቸዉ ተሰናብተዉ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ተተኪውን ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ብሔራዊ ምርጫ ይካሄዳል ሲል አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
