በዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።
የማንችስተር ዩናይትድን ግብ ጆሽዋ ዚርኪዜ ሲያስቆጥር ኦያርዛባል ሪያል ሶሴዳድን አቻ አድርጓል።
የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ቼልሲ ከኮቤንሀቨንን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የቼልሲን ግቦች ሬስ ጄምስ እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ ማስቆጠር ችለዋል።
በሌላ የዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቶተንሀም በአልክማር 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ውድድር መድረኮች ምንም ጨዋታ ያልተሸነፉ ቡድኖች ሆነው ቀጥለዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
