አንጋፋው የማሲንቆና በገና ተጫዋች ድምጻዊና የሙዚቃ መምህር አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ግጥምና ዜማ በመድረስ ክራር ፣ በገና እና ማሲንቆ በመጫወት የሚታወቁት አለማየሁ ፋንታ ፤ ለበርካታ ዓመታት በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤትም በመምህርነት አገልግለዋል፡፡

በተለየ የማሲንቆ አጨዋወታቸው የሚታወቁት አለማየሁ ፋንታ፤በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅ የቻሉ ናቸዉ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ባወጣው የሀዘን መግለጫ ፤ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ማህበረሰብና ለመላው ሕዝብ ከባድ ሀዘን ነው ብሏል፡፡

በነገው ዕለት የአስክሬን ሽኝት መርሐ-ግብር ተደርጎ ስርዓተ ቀብራቸው ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈጸም ለማወቅ ችለናል፡፡

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *