የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ቀጠናዊ ጉዳዩ ላይ ለመምከር እና በባህል ለማስተሳሰር ያግዛል የተባለ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነዉ ተብሏል ።
ይህን የገለፀዉ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዝግጁቱን አስመልክቶ ባዘጋጀው መድረክ ነዉ።
ለሁለተኛ ጊዜ የሚዘጋጀው ይህ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የባህል እና ጥበብ ፌስቲቫል የቀጠናዉን ሀገራት ማህበረሰብ ትስስር ለማሳደግ እንደሆነ ተገልፆል።
በቀጠናዉ አስራ ስምንት ሀገራት ቢኖሩም ይህ ፌስቲቫል አስራ አንዱ የቀጠናዉን ሀገራትን ብቻ የሚያሳትፍ ነዉ ተብሏል።
ከመጋቢት 11እስከ 14 ይካሄዳል በተባለዉ ፌስቲቫል የቀጠናዉን ሀገራት ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባለፈ በባህል መደገፍ የሚያስችል ነዉ ሲል ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አስታዉቋል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለመፍጠር ባህልን እንደ ግንኙነት ድልድይ ለመፍጠር የታለመለት ዝግጅት መሆኑን ገልፆል ።
“ባህል እና ጥበባት ለቀጠናዊ ህዝብ ለህዝብ ትስስር” ፌስቲቫል ለአራት ቀናት ሲካሄድ ከጅቡቲ ÷ ታንዛኒያ ÷ ኬኒያ እና ሌሎች ሀገራት የባህል ትእይንቶች÷ የፊልም እና የመፅሐፍ አዉደርእይ ይዘዉ እንደሚቀርቡ ተገልፆል።
ቁምነገር አየለ
መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም
