የ1 ሺህ 446ኛው የሐጅና ዑምራ ጉዞ የምዝገባ ጊዜ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም መራዘሙን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የተራዘመው የምዝገባ ሒደት ከትናንት መጋቢት 2 ጀምሮ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ነው የተገለጸው፡፡

ምዝገባው የተሰጠው የጊዜ ገደብ በቂ አለመሆኑ በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ መራዘሙ ተገልጿል፡፡

ቀኑ የተራዘመው ፍላጎት ያላቸው ሐጃጆችን ለማስተናገድ በማለም መሆኑን የጠቆመው ምክር ቤቱ ÷ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በተሰጠው ጊዜ እንዲመዘገብ ጥሪ አቅርቧል።

መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *