በአዲስ አበባ ከተማ በነዋሪዎች በቀን 2ሺመቶ ቶን ቆሻሻ የሚመረት መሆኑን የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቋል ፡፡
በአማካይ በቀን አንድ ሰው 0ነጥብ49 ቆሻሻ ያመርታል ተብሏል።
በዚህ አመት ከተመረተው ቆሻሻ ውስጥ 12 በመቶ የሚሆነውን ቆሻሻ ወደ ሀብት መቀየሩን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ ተናግረዋል
4 ሺህ በሚሆኑ በተደረጁ ወጣቶች በመልሶ መጠቀም መንገድ እና ማዳበሪያ በሚያዘጋጁ ወጣቶች በኩል እንዲወገድ እየተደረገ መሆኑን ዶክተር እሸቱ ተናግረዋል።
ለዚህም ከ2መቶ 32 በላይ የመልሶ መጠቀሚያ ቦታዎችን ማዘጋጀት መቻሉን አንስተዋል፡፡
ኤጀንሲው በ 5 አመት እቅዱ ዉስጥ ቆሻሻን ወደ መልሶ መጠቀሚያ (recycling) ፓርክ የማቋቋም እቅድ እንዳለዉ ተገልጿል
በአዲስ አበባ ከተማ ፕላስቲክን እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል የሚሰሩ 15 ፋብሪካዎች አሉ ያሉት የኤጀንሲዉ ዋና ዳሬክተር በዚህም ኢትዬጵያ ቆሻሻን ኤክስፖርት በማድረግ ዶላር ማግኘት ችላለች ብለዋል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም
