አሜሪካ እና እስራኤል የሶስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ባለስልጣናትን በማነጋገር ከጋዛ በግዳጅ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን ለማስፈር መምከራቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የአሜሪካ እና የእስራኤል ባለስልጣናት ከሱዳን፣ሶማሊያ እና ከሶማሌላንድ ግዛት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል።
የሱዳን ባለስልጣናት ከአሜሪካ የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን እና የሶማሊያ እና የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ደግሞ ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
ነጩ ቤተመንግስት እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ ከሮይተርስ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጡም።
ከአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተቃራኒ ፤በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የአረብ መሪዎች ከግብጽ የቀረበላቸዉን ጋዛን መልሶ የመገንባት የ53 ቢሊየን ዶላር ዕቅድ ማጽደቃቸዉ ይታወሳል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
ሰንፔር እንዳለዉ
መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
