ሃማስ ድርድሩን ለመቀጠል ሸምጋዮች ያቀረቡትን ሃሳብ ተቀብሏል፡፡

ሃማስ የአሜሪካ ዜግነት ያለውን የእስራኤል ወታደር በመልቀቅ እና አራት የጥምር ሃገር ዜግነት ያላቸዉ እስራኤላውያንን አስከሬን በመመለስ ድርድሩን ለመቀጠል የቀረበዉን ሃሳብ ማፅደቁን አስታውቋል።

የሃማስ አመራር ድርድሩን ለመቀጠል ሃሙስ ዕለት ከአሸማጋዮች ጥያቄ ቀርቦለት የነበር ሲሆን፤ አርብ በጠዋት የቀረበዉን ሃሳብ በሃላፊነት እና በአዎንታዊነት ተቀብያለሁ ብሏል፡፡

ሃማስ በሰጠው ምላሽ ፤የአሜሪካ ዜግነት ያለው እስራኤላዊ ወታደር ኤዳን አሌክሳንደርን ለመልቀቅ እና ሌሎች አራት ጥምር ዜግነት ያላቸዉ እስራኤላዊያንን አስከሬን ለመመለስ መወሰኑን አስታዉቋል፡፡

ቡድኑ ድርድር ለመጀመር እና በሁለተኛው ምዕራፍ ጉዳዮች ላይ ሁሉን አቀፍ ስምምነት ለመድረስ ሙሉ ዝግጁ ነኝ ያለ ሲሆን፤ እስራኤልም ሙሉ ቃሏን እንድትፈጽም አሳስቧል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *