ዋና ጸሃፊዉ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በፍጥነት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ እና ታጋቾችም እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡
ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ከ4መቶ በላይ ፍልስጤማዊያን በተገደሉበት የእስራኤል የአየር ጥቃት ከፍተኛ ድንጋጤ እንደተሰማቸዉም ገልጸዋል፡፡
የጋዛ ባለስልጣናት እንደገለጹት የሟቾች ቁጥር ከ4መቶ ተሻግሯል፡፡
ሃማስ ከእስራኤል ጋር በጥር 19 ካደረገዉ የተኩስ አቁም ስምምነት በተጨማሪ ሁለተኛ ዙር ስምምነት ለማድረግ በንግግር ላይ የነበሩ ሲሆን፤ እስራኤል በድንገት ጥቃቱን ማድረሷ ተገልጿል፡፡
በጥቅምት 2023 በሁለቱ መካከል በተጀመረዉ ደም አፋሳሽ ጦርነት ፤ አብዛኛዉ ቁጥራቸዉ ሴቶች እና ህጻናት የሆኑ ከ48ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ህይወታቸዉ አልፏል፡፡
ጋዛም ወደ ፍርስራሽነት ተቀይራለች፡፡
ዓለምዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ እና በቀድሞ የጦር ሚኒስትራቸዉ ዮአቭ ጋላንት ላይ ለፈጸሙት የጦር ወንጀል የእስር ማዘዣ ማዉጣቱ ይታወሳል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም
