የዩኒሴፍ ሃላፊ ካትሪን ሩሴል፤ ጥቃቱን ተከትሎ የሚወጡ ዘገባዎች እና ምስሎች እጅግ ዘግናኝ ናቸዉ ብለዋል፡፡
እስራኤል ባደረሰችዉ ጥቃት በአንድ ቀን የደረሰ ከፍተኛዉ የህጻናት ሞት ተመዝግቧል ሲሉ ሃላፊዋ ተናግረዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ፤ ጥቃቱን በእጅጉ አዉግዞታል፡፡
ጥቃቶቹ እጅግ ዘግናኝ ናቸዉ፤ ከ1መቶ30 በላይ ህጻናትም ህይወታቸዉ አልፏል ሲሉ ሃላፊዋ ተናግረዋል፡፡
ጥቃቶቹ ህይወት ከመንጠቅ ባለፈ፤ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እያደረሰ ነዉ ብለዋል፡፡
ህጻናት እና ሴቶች ተኝተዉ የነበሩባቸዉ መጠለያዎች ጭምር ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ስለዚህ አሁን ላይ በጋዛ ምንም ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም ነዉ ያሉት፡፡
ሃላፊዋ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበው ሁሉም አካላት የተኩስ አቁም ስምምነቱን በአስቸኳይ እንዲቀበሉ እና ሁኔታው የበለጠ እንዳይባባስ ተፅእኖ ያላቸው ሀገራት ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡ እጠይቃለሁ ማለታቸዉን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም
