ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙትን የሃይል መጠን ወደ 50 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በዚህ ዓመት 55 አዳዲስ ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 120 ፋብሪካዎች ፍቃድ አውጥተው ስራ ለመጀመር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

አምራች ኢንዱስሪዎች በተደጋጋሚ ከሚያነሱት ጥያቄዎች መካከል አንዱ የሃይል አቅርቦት ነዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ችግር ለመፍታት በፊት ከነበረዉ የሃይል አቅርቦት ወደ 50 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉን አስታዉቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)አምራችን ኢንዱስትሪዎች ብቻ ሳይሆን በሃገር አቀፍ ደረጃ የሃይል አቅርቦትን ወደ 47 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ነዉ የገለጹት፡፡

ይህ ቁጥር በቂ ነዉ ማለት ባይቻልም የኢንዱስሪዎችን መስፋፋት እና የማምረት አቅም እንዲያድግ እንዲሁም የዜጎችን የሃይል ፍላጎት ለሟሟላት በየዓመቱ የሚያገኙትን የሃይል መጠን ማሳደግ ተገቢ ነዉ ብለዋል፡፤

ሆኖም ከዚህ በፊት ከነበረዉ የሃይል አቅርቦት የተሸሻለበት ዓመት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በምክር ቤት ቀርበዉ ከምክርቤቱ አባላት ለተነሱላቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

ልኡል ወልዴ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *