አለም አቀፍ የዳውን ሲንድረም ቀን የድጋፍ ስርአቶቻችን ይሻሻሉ በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለጸ ።

ቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ14ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ10ኛ ጊዜ መጋቢት 28 እንደሚከበር ፍቅር የኢትዮጵያ አእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር አስታውቋል ።

ቀኑን ለማክበርም አስፈላጊ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የገለጸው ማህበሩ በእለቱ ከ 2 ሰአት ጀምሮ የእግር ጉዞ እና የተለያዮ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ቀኑ ይከበራል ብሉዋል፡፡

የአእምሮ እድገት ውስንነትን በተመለከተ በሀገራችን ውስጥ ያለው የሰዎች የግንዛቤ ማነስ ትልቅ ችግር መሆኑን ማህበሩ የገለጸ ሲሆን የአእምሮ እድገት ውስንነት እንደሀገር ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብሉዋል ።

ቀኑም ሲከበር የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ትምህርት እንዲያገኙ እንዲሁም መብታቸው እዲከበር ለማስቻል መሆኑን ጨምሮ ገልጹል።

ፍቅር ኢትዮጵያዊ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር በ1987አ.ም የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ባላቸው ወላጆች የተቋቋመ ሀገር በቀል ማህበር ሲሆን በ9 ክልሎች እና በ18 ከተሞች ተደራሽ ነው፡፡

ማህበሩ ባጠቃላይ ከ16 ሺ በላይ ለሚሆኑ አባላቶች የተለያዩ ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ላይ እደሚገኝ አስታውቁዋል፡፡

ዳወን ሲንድረም ዘላቂ የሆነ እና የአፈጣጠር የጤና እክል ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቀላል እሰከ ከባድ ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

ሐመረ ፍሬው

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *