ባንኩ ከዚህ ቀደም ለሀገር አበርክቶ ያላቸዉ እንስቶች ስም ብቻ 206 ቅርንጫፍ እየሰየመ ቆይቷል።
ባንኩ አዲሱን “እማዬ” የተባለ አዲሱ ቅርንጫፍ የድካማቸዉን ያህል ያልተነገረላቸዉን እናቶች ዉክልና እንዲኖራቸዉ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልፆል።
ከባንክ ግልጋሎት በተጨማሪ ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡበት የባንኩ አዲሱ ቅርንጫፍ ልጆች ለእናቶቻቸዉ ልዩ ልዩ ኘሮግራሞችን በነፃ ማከናወን የሚችሉበት ነዉ ተብሏል።
እናት ባንክ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና የአቅም ዉስንነት ለመቅረፍ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፆል።
ባንኩ በሶስት የብድር አማራጮች ብድር እየሰጠሁ ነዉ ብሏል።
በዚህም ባንኩ ከአራት ወራት በፊት በጀመረዉ ማለፊያ የተሰኘ የዲጂታል መተግበሪያ ከሀያ ሺህ ብር በላይ ብድር መስጠቱን እና ሰባ ሺህ ያህል ትራንዝአክሽን መፈፀሙን ተናግሯል።
እናት ባንክ ዛሬ በከፈተዉ ልዩ ቅርንጫፍ ምክንያት አድርጓ በልዩ ሁኔታ የፅሁፍ ዉድድር ለማድረግ ማሰቡን አስታዉቋል።
በቀጣዩቹ አስር ቀናት ለዚህ ዉድድር የፅሁፍ ስራዎችን ወደ አዲሱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ማስገባት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
የዘንድሮው አመት የፅሁፍ ዉድድር መዝጊያ የእናቶች ወር በሆነዉ የግንቦት ወር መጀመሪያ እንደሚደረግ ተገልፆል።
ቁምነገር አየለ
መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም
