ለ1መቶ54 ሴት ስራ ፈጣሪዎች ከ55 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ያለምንም ማስያዣ በዝቅተኛ ወለድ መስጠቱን አስታውቋል።
ማርች 8 የሴቶች ቀንን አስመልክቶ እስከ መጋቢት 22 ቀን የሚቆይ “እችላለሁ” የሚል መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።
ከመርሐግብሩ አንዱ የሆነው የኤግዚቢሽን እና ባዛር በዛሬው ዕለት ተከፍቷል።
ከባንኩ ብድር ወስደው ስራ የጀመሩ ስራ ፈጣሪ ሴቶች ንግዳቸውን የሚያስተዋውቁበት እንዲሁም የገበያ ትስስር የሚያደርጉበት መሆኑ ተገልጿል።
ባዛሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 19 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል።
ባንኩ የዛሬውን ሳይጨምር ለ1መቶ54 ስራ ፈጣሪ ሴቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም ገልጿል።
የዚህኛው ዙር የ”እችላለሁ” መርሐግብር ለ 4ኛ ጊዜ የተዘጋጀ ነው።
እስከዳር ግርማ
መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም
