የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት በቤት ዉስጥ እስር መሆናቸዉ ተነገረ፡፡

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የቤት ዉስጥ እስር እንደተፈረደባቸዉ ፓርቲያቸዉ አስታዉቋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩን ጨምሮ በከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣናት የተመራ የታጠቁ ሃይሎች በዋና ከተማይቱ ጁባ ወደሚገኘው ማቻር መኖሪያ ቤት በመግባት ጠባቂዎቻቸውን ትጥቅ እንዲፈቱ ማድረጋቸዉን የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ ኦፒዲኦ አስታዉቋል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንቱ አሁን ላይ በቤት ዉስጥ እስር ላይ ቢሆኑም የጸጥታ ሃይሎች ግን ሊወስዷቸዉ ሞክረዉ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የአገሪቱ መንግስት በጉዳዩ ላይ አስተያየት አልሰጠም ሲል ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

እስከዳረ ግርማ

መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *