በጋዛ ያለዉ ሰብዓዊ ሁኔታ እጅጉን ተባብሷል ያለዉ ድርጅቱ፤ 1መቶ42 ሺህ ፍልስጤማዊያን ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡
የእስራኤል የጋዛ ነዋሪዎችን ከስፍራዉ የማስወጣት ትዕዛዝ የጋዛን 17 በመቶ ሲይዝ፤ በግምት 61 ካሬ ኪሎሜትር ይሸፍናል ተብሏል፡፡
የማያቋርጥ የቦምብ ድብደባ፣ዕለታዊ የማፈናቀል ትዕዛዝ፣ ወደ ጋዛ በሚገቡ ጭነቶች ላይ ያለው እገዳ እንዲሁም ወደ ጋዛ የሚደረጉ ሰብዓዊ እንቅስቃሴዎችን ማገድ በጠቅላላው ከ2 ሚሊየን በላይ በሚሆነው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ተናግረዋል፡፡
በጋዛ ሁሉም ነገር እያለቀ ነው – የድጋፍ አቅርቦቶች፣ ጊዜ እና ህይወት በጋዛ እያለቁ ነዉ ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ነዋሪዎች በሕይወት የሚተርፉበት ቦታ ቀን በቀን አዲስ የእስራኤል የማፈናቀል ትእዛዝ በወጣ ቁጥር እየጠበበ መምጣቱን ጠቁመዋል።
በአንድ ሳምንት ብቻ ከ1መቶ42ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፤ ይህ ቁጥር በሚቀጥሉት ቀናት ይጨምራል ብለዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም
