ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከየትኛውም ሃገር ወደ አሜሪካ በሚገባ መኪና እና የመኪና መለዋወጫ ላይ 25 በመቶ ታሪፍ እንደጣሉ የገለጹ ሲሆን የፕሬዝዳንቱ እርምጃ የእንግሊዝን የተሸከርካሪ ኢንደስትሪዎች ክፉኛ እንደሚጎዳ ተገልጹል፡፡
በዚህም የእንግሊዙ ቻንስለር ራቼል ሬቪስ ለስካይ ኒውስ እንደገለጹ የትራምፕ ውሳኔ በእንግሊዝ የዋጋ ግሽበትን በማባባስ ኢኮኖሚውን የሚጎዳ ነው ብለዋል፡፡
ቻንስለር ራቼል ሬቪስ አክለውም የንግድ ጦርነት ለየትኛውም አካል የሚበጅ አይደለም ብለዋል፡፡
ራቼል እንዳሉት ከአሜሪካ ጋር ያለንን የቆየ የንግድ መልካም ግንኙነት የምናጠናክርበትን መንገድ እያየን ነው ፡፡ በምናደርጋቸው ውይይቶችም በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚሆነውን እናያለን ብለዋል፡፡
ትራምፕ በበኩላቸው እርምጃቸው የ አሜሪካንን የተሸከርካሪዎች ኢንደስትሪን ለማሳደግና የበለጠ እድል ለመስጠት እንደሆነ የገለጹ ሲሆን ለዚህም ከፍተኛ በጀት መመደቡን ስለማንሳታቸው የዘገበው ስካይ ኒውስ ነው ፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
