ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል የተቃረበው የሊቨርፑል ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ ሎስ ብላንኮዎቹን ለመቀላቀለ ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።
ማሪንጌዎቹ አርኖልድ የአለማችን ምርጡ የቀኝ መስመር ተጨዋች እንደሆነ እንደሚያምኑ ተነግሯል።
አሌክሳንደር አርኖልድ በሪያል ማድሪድ ቤት ትልቅ ክፍያ እንደማይቀርብለት ሲገለፅ ደሞዙ እንደ ቪንሰስ እና ምባፔ ጋር እንደማይሆን ተገልጿል።
ሪያል ማድሪድ ለአርኖልድ ቡድናቸውን መቀላቀል ከፈለገ የሚያቀርቡለትን ውል ብቻ መቀበል እንዳለበት ከጅምሩ ማሳወቃቸው ተዘግቧል። አርኖልድ የሪያል ማድሪድን ውል ካልተቀበል የሚፈልገውን ማድረግ እንደሚችል እንደገለፁለት ሲነገር አርኖልድ በበኩሉ የሎስ ብላኖኮዎቹን ሀሳብ መቀበሉ ተገልጿል።
አርኖልድ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል በመስማማቱ ሂደት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ጁድ ቤሊንግሀም መሆኑ ተጠቁሟል። እንግሊዛዊው ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም አርኖልድ ሪያል ማድሪድን እንዲቀላቀል ለማሳመን ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።
አርኖልድ በአንድ ወቅት የእግር ኳስ ዘመኔን በሊቨርፑል መጨረስ እፈልጋለሁ እንደዛ የማደርግም ይመስለኛል ሲል ተናግሯ ነበር። አሁን ላይ ታዳያ የሊቨርፑል ድጋፊዎችን ለብሰጨት የዳረገው ተጨዋቹ የውደደር አመቱ ሳይጣናቀቅ ይሄን ውሳኔ መውሰኑ ሆኖዋል።
የሚውዱትን የሃገራቸውን ልጅ አሁን ላይ ቀዩን ማለያ ለብሶ ኢንዲጨዋት አይፈልጉም ይባሰ በሎ የተጨዋቹን 66 ቁጥር ማልያ እያቃጠሉ እና ከሌጅንድነትም እያሰውጡት ነው ፡፡
ያም በ2010 የአርሰናል ደጋፊዎች በኒዘርላንዳዌው ሩብን ቫን ፔረሲ ወደ ማንቸሰትር ዩናይትድ ሲያምራ 10 ቁጥር ማለያው ላይ እንዳደረጉት ጉዳዩ ተመሳሳሰሏል።
ጋዲሳ መገርሳ
መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
