ኦቲዝም ላለባቸው ልጆች የመድኃኒት ዕጥረት አስቸጋሪ ሆኗል ተባለ።

በኦቲዝም ዙሪያ የሚሰሩ ማዕከላት በመድኃኒት ዕጥረት መቸገራቸውን ገልፀዋል።

ማዕከላቱ በቤት ኪራይ፣ መደበኛ ትምህርት ለማግኘት መቸገር እንዲሁም በመድኃኒት ዕጥረት እየተፈተኑ መሆኑን ሰምተናል።

ከዛሬ 18 አመት በፊት ከ15ሺህ ህፃናት አንዱ ከኦቲዝም ጋር ይወለድ ነበር፤ አሁን ላይ ከ36 ህፃናት አንዱ ከኦቲዝም ጋር ይወለዳል።

የችግሩ የመከሰት ዕድል ከፍተኛ ቢሆንም ተገቢው ትኩረት አልተሰጠውም ተብሏል።

ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል “በላቀ የአጋር ተሳትፎ አካላት ፣ አካታችነትን በማጎልበት በኢትዮጵያ የኦቲዝም ተቀባይነት እና አገልግሎት ተደራሽነት ማሻሻል” በሚል መሪ ቃል የኦቲዝም ወር ይከበራል።

በወሩም አለምአቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች መቀበል ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተገልጿል።

በተለያዩ የአገራችን ክልሎች የኦቲዝም ማዕከላት እየተገነቡ መሆኑንም ሰምተናል።

መቀሌ፣ ቡታጅራ፣ ወላይታ ሶዶን ጨምሮ 13 የኦቲዝም ማዕከላት ሊከፈቱ መሆኑም ተገልጿል።

በኒያ ፋውንዴሽን ስር የጆይ ኦቲዝም ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ስትራክቸራል ስራ ሙሉለሙሉ መጠናቀቁም ተገልጿል።

የኦቲዝም ወር በአገራችን ለ23ኛ ጊዜ በአለምአቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ ይከበራል።

ኒያ ፋውንዴሽን ከጤና ሚኒስቴር እና ነህሚያ ኦቲዝም ማዕከል ጋር በመተባበር የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *