የህክምና ባለሞያ እጥረት እንዳለበት የአራብሳ ጤና ጣቢያ ገለፀ

በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ አራት አራብሳ ጤና ጣቢያ ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ደያሳ ማእከሉ በአሁን ጊዜ 76ሺህ ለሚጠጉ የ አካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸው የባለሞያ እጥረት አለብን ብለዋል፡፡

በኮሪደር ልማት ምክንያት ከካሳንቺስ እና ከፒያሳ እንዲሁም ከሌሎች ቦታዎ የተነሱ ነዋሪዎች በመጨመራቸው በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ጫና የፈጠረ ሲሆን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጊዜያዊ ማስተንፈሻ ቦታዎችን እየሰራልን ይገኛል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ።

ምንም እንኳን አሁን ላይ የመድሃኒትና የህክምና መስጫ መሳሪያዎች እጥረት የለንም ከአገልግሎት ፈላጊው አንፃር ግን የህክምና ባለሙያ እጥረት መኖሩን አቶ ጌታሁን ደያሳ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በማእከሉ ድንገት ለሚከሰት ወረርሺኝ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን መቋቋሙን አቶ ጌታሁን ተናግረዋል።

አራብሳ ጤና ጣቢያ ከ270 በላይ በመደበኛ እና በተመላላሽ የሚያገለግሉ ሰራተኞች አሉት።

ልዑል ወልዴ

መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *