“በጎ እናድርግ፤ ፍቅራችንን እናካፍል” በሚል መሪ ቃል ለ10ኛ ጊዜ የፍቅር ሳምንት ሊከበር ነው፡፡

ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር ለ 8ቀናት የፍቅር ሳምንትን ሊያከብር መሆኑን አስታዉቋል፡፡

ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን ከጎዳና ተዳዳሪነት እና ዝቅተኛ ህይወት በማላቀቅ በራሳቸው እንዲቆሙ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

በማህበሩ ከሚከናወኑ ዝግጅቶች አንዱ የሆነዉ የፍቅር ሳምንት በዚህ ዓመት ከመጋቢት 28 እስከ ሚያዚያ 5 ድረስ እንደሚከበር አስታዉቋል፡፡

ማህበሩ ከ2007 ጀምሮ በየዓመቱ ለ 8ቀናት የፍቅር ሳምንትን ሲያከብር ቆይቷል፡፡

የፍቅር ሳምንት ሲከበር የማህበሩን የስራ እንቅስቃሴዎች መጎብኘት ዋነኛዉ አላማ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ1ሺህ2መቶ50 በላይ ህጻናት እና እናቶችን የያዘ ተቋም ነዉ፡፡

አፎሚያ አሸናፊ

መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *