የኒጀር ወታደራዊ መሪዎች የቀድሞ ሚኒስትሮችን ከእስር መልቀቃቸው ተዘግቧል፡፡

ከስልጣን የተወገዱት ፕሬዝደንት ሞሃመድ ባዙም ግን ከተለቀቁት ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ እንደሌሉ ተነግሯል፡፡

የኒጀር ወታደራዊ መሪዎች እ.ኤ.አ. በ2023 ያባረሩትን መንግስት የቀድሞ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ከ50 በላይ እስረኞችን መፍታታቸው ተዘግቧል፡፡

ከእነዚህም መካከል የቀድሞዎቹ የመከላከያ፣ የነዳጅ እና የፋይናንስ ሚኒስትሮች ይገኙበታል፡፡

ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ፍርድ የተፈረደባቸው ወይም ቀደም ሲል መፈንቅለ መንግስት አድርገዋል ተብለው የተከሰሱ ከተለቀቁት መካከል ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2023 ወዲህ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዙም ከእስር እንዲፈቱ አለም አቀፍ ጥሪ ቢቀርብም ከተፈቱት ሰዎች ዝርዝር ውስጥ እንዳልገቡ ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ቢቢሲ የፕሬዚዳንት ባዙም መታሰርን አስመልክቶ ለፍትህ ሚኒስትሩ አሊዩ ዳውዳ ጥያቄ አቅርቦ “የብሄራዊ ደህንነት እና ሉዓላዊነት” ስጋቶች ላመለቃቃቸው ምክንያት ነው ብለውኛል ብሏል፡፡

አዲሱ የኒጀር መሪ የቀድሞው የፕሬዚዳንቱ ክቡር ዘብ መሪ ነበሩ፡፡

ኒጀር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣች በኋላ አራት ጊዜ መፈንቅለ-መንግሥት አስተናግዳለች። ከፕሬዝደንት ባዙም በፊት የነበሩት ማሐሙዱ ኢሶፉ ክብር ዘቡን ያቋቋሙት ለዚህ ነበር፡፡

ፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙም ኒጀር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በጎሮጎሳውያኑ 1960 ነጻ ከወጣች በኋላ የአገሪቷን መሪ እንዲተኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡ መሪ ናቸው።

በአካባቢው ከሚገኙ ጽንፈኛ ታጣቂዎች ጋር በሚደረገው ውጊያም ምዕራባውያኑ እንደ ቁልፍ አጋር ይቆጥሯቸዋል።

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *