ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን ታሪፍ ይፋ ካደረጉ በኋላ የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት አገራት “የአጸፋ ምላሽ እንዳይሰጡ” አስጠንቅቀው፣ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ”በጸጋ እንዲቀበሉ” ተናግረዋል።
ብራዚል በትራምፕ የተጣለውን የ10 በመቶ ታሪፍ በመቃወም አዲስ ሕግ አጽድቃለች።
በላቲን አሜሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ብራዚል በትራምፕ የተጣለውን የ10 በመቶ ታሪፍ በመቃወም አዲስ ሕግ አጽድቃለች።
የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ” የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ የዓለም ንግድ ድርጅትን ጨምሮ የሁለትዮሽ ንግድ ውስጥ ያሉንን አማራጮች በሙሉ እንገመግማለን” ብለዋል።
ቻይና የዶናልድ ትራምፐን እርምጃ በመቃወም “ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ቆራጥ” መሆኗን ገልጻለች።
ይህ የቻይና የማስጠንቀቅያ ምላሽ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከመጋቢት 27 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሁሉም ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ታሪፍ መጣላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው።
ከመጋቢት 29/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ወደ 60 የሚጠጉ አገራት ከፍተኛ የሆነ ታሪፍ ተጥሎባቸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ እርምጃዎቹ ፍትሃዊ ባልሆኑ የንግድ ፖሊሲዎች ላይ የተሰጠ ምላሽ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም በውሳኔዎቹ “በጣም ቸር” ለመሆን መሞከራቸውን አብራርተዋል።
መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም
