በጤናው ዘርፍ ያለውን የሰው ሃይል ለመደገፍ 1.5 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉ የተደረገላቸው ተቋማት አብዛኛው ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች እና በአዕምሮ ጤና ላይ የሚሰሩ ሲሆን፤ በተለያዩ ውድድሮች ያለፉ ናቸው።

ይህም ከCOVID-19 ወረርሽኝ በኋላ የጤናዉ ዘርፍ እንዲያገግም ለመርዳት፣ የተሻለ እና የተረጋጋ የጤና ሥርዓት ለመገንባት እና የጤና ተደራሽነትን ለማገዝ ይረዳል ተብሏል።

ግሎባል ኸልዝ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ለ10 ወራት በጤናው ዘርፍ ያለውን የሰው ኃይል ለማጠንከር የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፍ አስታውቋል።

ድጋፉ በኢትዮጵያ፣ በማላዊ እና በሶማሊላንድ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ፣ አስር አጋሮች ከፍተኛ ፈንድ፤ እንዲሁም ሁለት አጋሮች አነስተኛ ፈንድ አግኝተዋል።

በዚህም ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ተደርጓል ነው የተባለው።
ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች እና በአዕምሮ ጤና ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች እና የጤና ማዕከላት ድጋፉ ይደረጋል።

የጤና ባለሙያዎች በብሔራዊ ደረጃ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የጤናዉ ዘርፍን ያጠናክራል ተብሏል።

የጤና ሰራተኞችን የመሪነት አቅም እና የፆታ እኩልነትን ለማሻሻል ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።
የጤና ባለሙያዎች ደህንነታቸዉ እንዲጠበቅ እና በዘርፉ እንዲቆዩ ድጋፍ ያደርጋሉ ነው የተባለው።

በብሪታኒያ የጤና እና ማህበራዊ እንክብካቤ ዲፓርትመንት የተደገፈ ሲሆን፤ ግሎባል ኸልዝ ደግሞ የፈንዱ አስተዳዳሪ ነው።

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *