ሌሴቶ በትራምፕ ከፍተኛ ታሪፍ የተጣለባት አፍሪካዊት ሀገር ሆናች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሌሴቶ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ50% ቀረጥ ጥለዋል።

ትንሿ ደቡብ አፍሪካዊት ሀገር ከአሜሪካ ጋር ባብዛኛው በአልማዝ እና በጨርቃጨርቅ፣ ጂንስን ጨምሮ ትልቅ የንግድ ልውውጥ አላት።

ትራምፕ በሁሉም ሀገራት ወደ አሜሪካ በሚያስገቡት ምርቶች ላይ ዝቅተኛው 10% የሆነ ታሪፍ ጥለዋል፡፡

በአፍሪካ በደርዘን ለሚቆጠሩ ሀገራት ከፍተኛ የተባለ ታሪፍ ይፋ አድርገዋል፡፡

ማዳጋስካር 47%፣ ሞሪሸስ 40%፣ ቦትስዋና 37% እና ደቡብ አፍሪካ 30% ታሪፍ የተጣለባቸው ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።

የናይጄሪያ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችም ላይ 14% ተጥሏል፡፡

ኬንያ፣ ጋና፣ ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሴኔጋል እና ላይቤሪያ ወደ አሜሪካ የሚላኩ ምርቶች በ10 በመቶ የመነሻ ታሪፍ ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል ይገኙበታል ሲል ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል።

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *