ከተመሰረተ አምስተኛ አመቱን እያከበረ የሚገኘው ቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ማህበረሰባዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡
እናቶች ከተረጂነት ወጥተው የሙያ ፤ የክህሎት ሥልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በመለስተኛ የንግድ ሥራ ዘርፍ ላይ እንዲሠማሩ እያደረገ መሆኑን ተናግሯል ቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ፡፡
በተለያየ ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ 20 /ሃያ/ ሕጻናትን ከመንግሥት ተቀብሎ በማዕከል ውስጥ በማሳደግና በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ለችግር የተጋለጡ 30 /ሠላሣ/ ሴቶች እናቶች/ በየወሩ ለ2 /ሁለት/ ዓመት የምግብ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የጤና ሽፋን ድጋፍ ሲያደርግላቸው መቆየቱም ቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተነግሯል፡፡
ለ58 ሃምሣ ስምንት/ ልጆቻቸው የትምህርት ቁሳቁስ በመስጠትና ዕድሜያቸው ለትምህርት ያልደረሱ ሕፃናትን በነፃ የሕፃናት ማቆያ /Day care/ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ላይም እገኛለሁ ብሏል፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን 30 /ሠላሣ/ እናቶች ከተረጂነት ወጥተው በራሳቸው ገቢ እንዲተዳደሩ ለማስቻል የተለያዩ የሙያ እና የክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ የገንዘብ፣ የማቴሪያል ድጋፍ በማድረግ እራሳቸው በመረጡት በመለስተኛ የንግድ ሥራ ዘርፍ ላይ እንዲሠማሩ ተደርጓል ተብሏል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም
