ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፍ ሁኔታዎች እንዲመቻች ተጠየቀ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን  በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙ  ወገኖች በምክክሩ እንዲሳተፉ የሚቻልበት ሂደት እንደሚቻች ለአማራ ክልል መንግስት ጥያቄ አቅርቢያለው  አለ፡፡

ኮሚሽኑ ይህን ይበል እንጂ   እስካሁን ይፋዊ መሆነ መልኩ  የተለየ ምላሽ ከክልሉ መንግስት አለማገኘቱን ጣቢያችን ሰምቷል፡፡

ኮሚሽኑ  በባህርዳር ከተማ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደቱን በመጭዉ ቅዳሜ እንደሚጀምር አስታዉቋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ፤  በክልሉ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደቱ እንዲዘገይ ምክንያት ከሆኑት ዉስጥ የፀጥታዉ ሁኔታ መሆኑን ገልጸዉ አሁን ላይ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸዉን አንስተዋል፡፡

በአለም አቀፍ ተሞክሮ ምክክር የሚካሄደዉ ፀጥታ በተሟላበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ባልተሟላበትም መካሄድ ይችላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ለክልሉ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙትና በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙት ወገኖች በምክክሩ እንዲሳተፉ የሚቻልበት ሂደት እንደሚቻች ጥያቄ ማቅረቡንና ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ አስታዉሰዉ እስካሁን ግን የተለየ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በክልሉ የሚካሄደዉ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ቢጠናቀቅም እንኳን ጥረቶች እንደሚቀጥሉና ከዚህ በኋላ የአጀንዳ የመቀበል ጉዳዮችን እንደሚቀጥሉና እንደሚያስተናግዱ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከመጪው ቅዳሜ መጋቢት 27ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በባህርዳር ከተማ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ካስታወቀ በኋላ የሚቀረዉ የትግራይ ክልል ይሆናል፡፡

ለአለም አሰፋ

መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *