የእስራኤል ጦር ዛሬ እንዳስታወቀው በደቡባዊ ሊባኖስ ሲዶን ግዛት ውስጥ ሃሳን ፋርሃት የተባለ የሃማስ ታጣቂ ቡድን አዛዥ መግደሉን ገልጹዋል፡፡
የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው እስራኤል በሲዶን ግዛት በሚገኝ ህንጻ ላይ በፈጸመችው ጥቃት የሶስት ሰዎች ሂወት ማለፉን አስታውቁዋል፡፡
የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም ቢሮ እንደገለጸው የእስራኤል ጥቃት ባለፈው አመት በአሜሪካ አደራዳሪነት በእስራኤልና ሄዝቦላህ መሃል የተፈጸመውን የተኩስ አቁም ስምምነት ህግ የጣሰ ነው ብሉዋል፡፡
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የተኩስ አቁም ስምምነቱ በእስራኤል እየተጣሰ እንደሆና በሄዝቦላህ ይዞታ ስር በሚገኙት የቤሩት ደቡባዊ ክፍሎች ላይ በእስራኤል
የሚፈጸሙት የሮኬት ጥቃቶች እየጨመሩ እደሚገኝ የሊባኖስ የጠቅላይ ሚንስተሩ ጽፈት ቤት ስለመግለጹ የዘገበው ዘ ስትሬት ታይምስ ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም
