በማንችስተር ሲቲ ስኬታማ አመታትን ያሳለፈው ኬቨን ዴ ብሩይን በዓመቱ መጨረሻ ከክለቡ እንደሚለቅ ይፋ አድርጓል።
ተጫዋች በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ላይ ባሰፈረው መልዕክት ሁሉም ታሪክ ፍፃሜ አለው ግን ይህ ምዕራፍ ያለ ምንም ጥርጥር ምርጡ ነው ብሏል።
የ33 ዓመቱ ተጫዋች በማንችስተር ሲቲ ቀሪዎቹ ወራት የመጨረሻዎቹ መሆኑን በመግለፅም በክለቡ ዙሪያ ያሉትን ሁሉ አመስግኗል።
ዴ ብሩይን በ10 አመታት የሲቲ ቆይታው 413 ጨዋታዎች ያደረገ ሲሆን 106 ግቦችን አስቆጥሮ 174 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
አንድ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና ስድስት የፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ 16 ዋንጫዎችን አሸንፏል።
ጋዲሳ መገርሳ
መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም
