ከዚህ ቀደም ቻይና የ34 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ አድርጋ የነበር ሲሆን፤አሜሪካ ዛሬ ማለዳ በቻይና ላይ 104 በመቶ ታሪፍ ጭማሪ ማድረጓን ተከትሎ ታሪፉን ከፍ አድርጋዋለች፡፡
ሁለቱ አገራት ወደ ንግድ ጦርነት እንዳይገቡ ስጋቶች የነበሩ ቢሆንም፤ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገዉ የቻይና የ84 በመቶ ታሪፍ የንግድ ጦርነቱን አስጀማሪ ነዉ ተብሏል፡፡
ትራምፕም ሆነ አስተዳደራቸዉ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገባቸዉ አገራት ዉሳኔዉን በጸጋ እንዲቀበሉ ማሳሰባቸዉ ይታወሳል፡፡
እንደ ቻይና እና ብራዚል ያሉ አገራት ጉዳዩን እንደማይቀበሉት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡
አሜሪካ ታሪፍ ጭማሪ ማድረጓን ተከትሎ ቻይና ተመሳሳዩን እርምጃ የወሰደችበትን ውሳኔ እንድትቀለብስ እስከ ዛሬ ረቡዕ ድረስ ቀነ ገደብ አስቀምጠዉ ነበር፡፡
ቻይና በበኩሏ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ በሚል አሜሪካ ለጣለችባት የታሪፍ ጭማሪ የአጸፋ ምላሽ ሰጥታለች፡፡
ትራምፕ ከቻይና በተጨማሪ በ60 አገሮች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ዛሬ ተግባራዊ አድርገዋል፡፡
ትራምፕ ቤጂንግ ከዋሽንግተን ጋር ስምምነት ላይ እስክትደርስ ድረስ አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለቻቸው ቀረጦች ተግባራዊ ሆነው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል፡፡
ሰንፔር እንዳለዉ
ሚያዚያ 01ቀን 2017 ዓ.ም
