3ኛዉ የአፍሪካ ብየዳ ጉባዔና ዓለም አቀፍ ኮንፈረስ በአዲስአበባ ሊካሄድ ነዉ

ከፊታችን ሰኞ ሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአዲስአበባ ይካሄዳል ።

በጉባኤው እና ኮንፈረንሱ ላይ ከ 16 የአፍሪካ ሃገራት በተዉጣጡ 43 የብየዳ ክህሎት ባለሙያዎች የብየዳ ዉድድር እንደሚካሄድ ተገልጿል ፡፡

በውድድሩ ኢትዮጵያ በአራት ሴትና በ19 ወንድ በአጠቃላይ በ21 ተወዳዳሪዎች እንደምትወከል በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልኅቀት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰላሙ ይስሃቅ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ከአፍሪካ ውጭ ከሚገኙ ስድስት ሀገራት የሚመጡ የብየዳ ባለሙያዎችና የዘርፉ ዓለም አቀፍ ተቋማት አመራሮች በጉባዔው እንደሚሳተፉ ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ተናግረዋል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *